Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በቱርክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ ልዑካን ቡድን በቱርክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በአንካራ ቆይታቸውም ከቱርክ አቻቸው ያሳር ጉለር ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቱ የጋራ የመከላከያ ትብብር ጉዳዩችና በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በትኩረት መምከራቸውን በቱርክ የኢትዮጵያ ኤንባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version