Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሰላም ስምምነቱ ኢትዮጵያውያን በመነጋገር ችግሮቻቸውን መፍታት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ መሆኑ ተገለጸ

አዲ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግስትና በህወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ኢትዮጵያውያን ችግሮቻቸውን በመነጋገር መፍታት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ መሆኑን የሰላም ሚኒስትር ገለጸ፡፡

የሰላም ሚኒስቴርና በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች “የሰላም ስምምነቱ ለአብሮነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ሐሳብ እየመከሩ ነው፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ጥፋት ከሚያስከትሉ ተግባራት በመራቅ ለልማታችን በጋራ መስራት አለብን ብለዋል፡፡

ከዚህ አንጻር የደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት በኢትዮጵያ ታሪክ ግጭትን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት በኩል አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ግጭትና አለመግባባትን በማስቀረት ሁላችንም ለሀገራችን ሰላም ቅድሚያ እንስጥ ያሉት አቶ ታዬ÷በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና እንዲሰፍን ሁሉም የሰላም ስምምነቱን በማጽናት ለሰላምና አብሮነት እንዲሰራ ጠይቀዋል።

Exit mobile version