Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የወጋገን ባንክ መቀሌ ከተማ የሚገኙ ቅርንጫፎች ዳግም ስራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጋገን ባንክ በመቀሌ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ 28 ቅርንጫፎች ዳግም አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታውቋል፡፡
 
የወጋገን ባንክ ማርኬቲንግ እና ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አፈወርቅ ገብረጻዲቅ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ባንኩ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በግጭት ምክንያት ስራ አቁመው የቆዩ ቅርንጫቹን ዳግም ስራ እያስጀመረ ነው፡፡
 
የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በተለይም በሽረ ዲስትሪክት የሚገኙ 17 ቅርንጫፎች ከዚህ በፊት ስራ መጀመራቸውን ነው የገለጹት፡፡
 
በዛሬው ዕለትም በመቀሌ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ 28 ቅርንጫፎች ዳግም አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
Exit mobile version