Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መልካም ዕሴቶችና ባሕሎችን ከውጪ ከሚመጣ የባሕል ወረራ መጠበቅ ይገባል – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀገሪቱን መልካም ዕሴቶችና ባሕሎች ከውጪ ከሚመጣ የባሕል ወረራ በመጠበቅ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ።

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በመጤ ባሕሎችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ላይ በጋምቤላ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂደዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በመድረኩ እንደተናገሩት ÷ መልካም ዕሴቶችና ባሕሎች ከውጪ ከሚመጣ የባሕል ወረራ በመጠበቅ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል፡፡

የክልሉ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ክርምስ ሌሮ ÷ ሀገሩንና ባሕሉን የሚወድና የሚጠብቅ ዜጋ ለመገንባት የባሕል ዕሴቶች ልማት ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ ሉላዊነትን መሰረት ያደረጉ የባሕል ወረራዎች የሚያሳድሩት ተጽእኖ ከፍተኛ በመሆኑ ኅብረተሰቡን በዘላቂነት ማስተማር እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች መጤ ባሕሎችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሕዝቡን መልካም ዕሴቶችና ባሕሎች እንዳይሸረሽሩም ኅብረተሰቡ መወያየት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version