Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ኢሳያስ ጅራ የሴካፋ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ የምሥራቅ እና መካከከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ፡፡
የሴካፋ የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔ በዛንዚባር የአባል ሀገራት እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተካሄዷል።
በዚህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ በድጋሚ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት የሴካፋ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ መመረጣቸውን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አቶ ኢሳያስ ከፈረንጆቹ 2018 ጀምረው ሴካፋን በምክትል ፕሬዚዳንት በመምራት ላይ ይገኛሉ።
በተመሳሳይ የታንዛንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዋላስ ካሪያ በድጋሚ በፕሬዚዳንትነት መመረጣቸው ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version