Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተለያዩ ሀገራት ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውስትራሊያ ኤምባሲ ፥ የኢትዮጵያ ገና በዓልን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚያከብሩ ሁሉ እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

የእንግሊዝ እና የዩክሬን ኤምባሲዎች ለሁሉም ኢትዮጵያውያን በተለይ በዓሉን ለሚያከብሩ መልካም በዓል እንዲሆን እንመኛለን ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኘው የካናዳ ኤምባሲ በዓሉ በረከትንና ደስታን ለኢትዮጵያውያን ይዞ የሚመጣ እንዲሆን ምኞቱን ገልጿል፡፡

የሞሮኮ ኤምባሲም ለመላው ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች የመልካም በዓል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በተመሳሳይ የስዊድን፣ ኢንዶኒዥያ፣ ጀርመን፣ ፖላንድ እና ሌሎች ኤምባሲዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Exit mobile version