Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዋሊያዎቹ በአቋም መፈተሻ ጨዋታ በሞሮኮ አቻቸው 2 ለ 1 ተሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሁለተኛ ዙር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በሞሮኮ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

የቻን ዝግጅቱን በሞሮኮ ካዛብላንካ በማድረግ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን በዛሬው ዕለት ከሞሮኮ አቻው ጋር ራባት በሚገኘው መሐመድ 6ኛ አካዳሚ አድርጓል፡፡

በጨዋታውም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት መሸነፉን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ቀደም ሲል ባደረገው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በሞሮኮ አቻው 1 ለ 0 በሆነ ውጤት መሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

በሀገር ውስጥ ሊግ የሚገኙ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ሰባተኛው የቻን እግር ኳስ ውድድር በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ከጥር 5 እስከ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።

Exit mobile version