Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ባይደን በካሊፎርኒያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከሣምንት በላይ ያስቆጠረውን ከባድ ውሽንፍር እና የጎርፍ አደጋ ተከትሎ በካሊፎርኒያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታወጀው፥ ውሽንፍሩን ለመቆጣጠር እና በአደጋው ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በካሊፎርኒያ ከሣምንት በላይ ባስቆጠረው ከባድ ውሽንፍር እና የጎርፍ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

እንዲሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋረጠባቸው አርቲ ዘግቧል።

Exit mobile version