Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ152 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ152 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የኩምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
 
ኮሚሽኑ ከታህሳስ 21 ቀን እስከ 27ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 61 ነጥብ 1 ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 91 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙት፡፡
 
ከተያዙት እቃዎች ውስጥም አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ አደንዛዥ እጾችና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
 
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ መያዛቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 111 ግለሰቦች እና ሰባት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version