Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ግብር ከፋዮች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዲከፍሉ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብር ከፋዮች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግብራቸውን እንዲከፍሉ እየተሠራ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በሚኒስቴሩ የታክስ ሥርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሥፋዬ ቱሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ግብር ከፋዮች በሥራ ቦታቸው ሆነው ጊዜንና ገንዘብን በቆጠበ መልኩ እንዲከፍሉ የሚያስችሉ አሠራሮችን እየተዘረጉ ነው፡፡

ላለፋት 15 ዓመታት ተግባራዊ ሲደረግ የነበረውን የታክስ አስተዳደር ሥርዓት ለመቀየርና ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም በሚቀጥሉት ሦስት ሣምንታት ዓለም አቀፍ ጨረታ እንደሚወጣ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ግብር ከፋዮች ባሉበት ቦታ ሆነው ግብራቸውን እንዲያሳውቁና እንዲከፍሉ የሚያደርግ ኢ- ታክስ የተባለ አሠራር በተግባር ላይ መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡

በሚቀጥሉት ሦስት ሣምንታትም በቴሌ ብር ግብር እንዲከፈል የሚደረግበት ሥርዓት ወደ ሥራ እንደሚገባ ሚኒስትር ዲኤታው ተናግረዋል።

ግብር ከፋዮች እነዚህን መንገዶች በመጠቀም ግራቸውን እንዲከፍሉ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል ብለዋል፡፡

ሙሉቀን አበበ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version