Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቴዎድሮስ ምህረት ከበደ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቴዎድሮስ ምህረት ከበደ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ በስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡ ሹመቶችን መርምሮ እያፀደቀ ነው፡፡

በዚህም አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከበደ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ሲሾሙ ወይዘሮ አበባ እምቢያለ መንግስቴ ደግሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል፡፡

ተሿሚዎች በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።

በአዲሱ ሙሉነህ

Exit mobile version