Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምዕራባውያን ለዩክሬን መሣሪያ ማቀበላቸውን ከቀጠሉ ዓለም አቀፍ ውድመት ሊከሰት እንደሚችል ሩሲያ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያኑ ለዩክሬን መሣሪያ ማቀበላቸውን የሚገፉበት ከሆነ ዓለም አቀፍ ውድመት ሊከሰት እንደሚችል የሩሲያ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ቪያቼስላቭ ቮሎዲን አስጠነቀቁ።

አፈ ጉባኤው ምዕራባውያን ሀገራት ለዩክሬን በሚያደርጉት ድጋፍ የሩሲያ የሩሲያ ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ከወደቀ ሞስኮ ኃይለኛ የጦር መሣሪያዎችን በመጠቀም አፀፋዊ ምላሽ ትሰጣለችም ነው ያሉት።

ዩክሬን ከአሜሪካ እና ኔቶ አባል ሀገራት በሚቀርብላት የጦር መሣሪያ ድጋፍ ንፁሐን የሚኖሩባቸውን አካባቢዎች ወደ ፍርስራሽ እየቀየረች ነው ብለዋል፡፡

ቮሎዲን ኪየቭ ይባስ ብሎ ድንበራችንን ለመግፋት እየሞከረች ነው ሲሉም ነው የጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ አፅንዖት የሠጡት፡፡

አንድ የሩሲያ ከፍተኛ ኅግ አውጪም ለዩክሬን የሚደርሰው የምዕራባውያኑ ድጋፍ በዚሁ ከቀጠለ እንደ እስካሁኑ በቸልታ እንደማይታለፍ ማስጠንቀቃቸውን አር ቲ ዘግቧል።

ቮሎዲን ማስጠንቀቂያ አዘል አስተያየታቸውን ለምዕራባውያኑ ያደረሱት ለኪየቭ የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማጠናከር ጀርመን በሚገኘው ራምስቴይን የተሠኘ የአሜሪካ አውሮፕላን ማረፊያ ተሰብስበው ከመከሩ እና ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version