Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጉብኝት አደረጉ፡፡

ፕሬዘዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ÷ ሆራይዘን አዲስ ጎማ ጥራት ያላቸውን የተለያዩ ጎማዎችን ለማምረት እያደረገ ያለውን ጥረት በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሆራይዘን አዲስ ጎማ እየሠራ ያለው ሥራ ለሌሎች አምራች ኢንዱስትሪዎች ዓርዓያ የሚሆን ነው ሲሉም አውስተዋል፡፡

ድርጅቱ ለጥራት ትኩረት በመስጠት የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳሰቡት ፕሬዚዳንቷ÷በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በሆራይዘን አዲስ ጎማ ተገኝተው የጎበኙት ድርጅቱ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችለውን የጥራት መስፈርቶች በማሟላቱ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዓለም አቀፍ የልኅቀት ሞዴል መሠረት አድርጎ ባዘጋጀው የጥራት ሽልማት ውድድር ሆራይዘን አዲስ ጎማ ለተከታታይ ሦስትጊዜያት የጥራ ሽልማት ውድድሮችን የሁለተኛ ደረጃ የልህቀት ዋንጫ ማሸነፉ ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version