Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት አቅሙን ለማሳደግ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተማሪዎችን ለማብቃትና የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ ድጋፍ እንዲደረግለት የደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡

የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር አቶ ፍቅር በላይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ ትምህርት ቤቱ በወቅታዊ ችግርና በተለያዩ ምክንያቶች ቢያልፍም ከሀገሪቱ ከፍተኛውን ውጤት በማስመዝገብና ተማሪዎችን በማብቃት ቀዳሚ መሆን ችሏል።

ሆኖም ትምህርት ቤቱ የበለጠ እንዳይንቀሳቀስ የመምህራን ዝቅተኛ የኢኮኖሚ አቅም፣ በቂ የሕክምና መገልገያዎችና ሥፍራዎች እጥረት ፣ የባለሙያ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የህንጻ  አገልግሎት እጥረትና  መሰል ችግሮችን ጠቅሰዋል፡፡

ወደፊት ትምህርት ቤቱን ለማሳደግና የበለጠ ተፎካካሪ እንዲሆን እንዲሁም ችግሮቹን ለመፍታት ሁሉም አካል በመተባበር መስራት እንዳለበትም ነው ያነሱት።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላይ ውጤታማ የሆነው የደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት ከዚህ በላይ መስራት እንዲችልና የቅበላ አቅሙን ከፍ አድርጎ ውጤታማ ተተኪ ትውልድን ለመፍጠር ሁሉም እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።

 

በከድር መሀመድ

 

 

Exit mobile version