Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤኒሻንጉል ከ13 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ከ13 ቢሊየን 285 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ መስጠቱት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቢሮው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ከተማ ካሳ በተጠናቀቀው ስድስት ወር 13 ቢሊየን 285 ሚሊየን 304 ሺህ ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 620 አልሚዎች ፈቃድ መሰጠቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ፈቃድ የተሠጠባቸው ዘርፎችም÷ ግብርና፣ ሆቴልና ቱሪዝም፣ ማዕድን፣ አገልግሎት ዘርፍ፣ ማምረቻ እና ኮንስትራክሽን መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡም ከ21 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ ነው ያሉት።

ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ከ5 ቢሊየን 808 ሚሊየን 355 ሺህ ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 190 አልሚዎች ፈቃድ መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡

በንጽጽር ሲታይም በአልሚዎች ቁጥር በ430 እንዲሁም በካፒታል መጠን ደግሞ ከ7 ቢሊየን 476 ሚሊየን 948 ሺህ ብር በላይ ብልጫ ማሳየቱን ጠቅሰዋል።

ይህም በክልሉ ያለው የኢንቨስትመንት ፍሰት በየዓመቱ እየጨመረ መሆኑን ያሳያል ነው ያሉት አቶ ከተማ፡፡

ግብርና፣ ማዕድን፣ ማምረቻ እና አገልግሎት ዘርፎች በልዩ ሁኔታ ቅድሚያ የሚሰጥባቸው ዘርፎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version