Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሐረሪ ብሄራዊ ጉባኤ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ብሄራዊ ጉባኤ 6ኛ ዙር 2ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩም የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የሐረሪ ብሄራዊ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ፣ ምክትል አፈ -ጉባኤ ወይዘሮ ዚነት ዩሱፍን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

እየተካሄደ በሚገኘው መደበኛ ጉባኤም የክልሉ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም እንዲሁም የትምህርት ዘርፍ የ2015 የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም በመገምገም የተለያዩ የትኩረት አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በጉባኤው የተለያዩ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version