Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዓመታዊው የአሆላሌ ፌስቲቫል ከነገ ጀምሮ በደሴና ሃይቅ ከተሞች ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓመታዊው የአሆላሌ ፌስቲቫል ነገን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በደሴና ሃይቅ ከተሞች ይካሄዳል፡፡

በፌስቲቫሉ በደቡብ ወሎ ዞን ያሉ ሁሉም ወረዳዎች እንዲሁም የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ሰሜን ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞንና ከተማ አስተዳደሮች በተጋባዥነት ይሳተፋሉ፡፡

የበርካታ ክዋኔዎች ድምር የሆነው አሆላሌ ባህላዊ ክዋኔ ማህበረሰቡ ለዘመናት ጠብቆ ሳይበረዝና ሳይደበዝዝ ላዛሬ እንዳደረሰው የዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ መስፍን መኮንን ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

ይህንን በጎ አጋጣሚ በመጠቀም ባህላዊ ክዋኔውን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ይሰራልም ነው ያሉት፡፡

በፌስቲቫሉ ከ35 ሺህ በላይ ታዳሚዎች የሚሳተፉ ሲሆን÷ ባህላችን ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል፡፡

በኢሳያስ ገላው

Exit mobile version