Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለሰላም ላበረከተችው አስተዋጽኦ ዕውቅና ተሰጣት

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በኢትዮጵያ የሰላም ድምፅ በመሆን ላበረከተችው አስተዋጽኦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰብ በሚል ዕውቅና ሰጥቷታል።

ኢጋድ ሦስተኛውን የድርጅቱ ዓመታዊ ሪፓርት በኬንያ ሞምባሳ እየገመገመ ይገኛል።

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፣ ቀጣናው በሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች በተፈተነባቸው ያለፉት ዓመታት የተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት የማይተካ ሚና ተጫውተዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version