Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ አሁን ባለው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
ከዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር ያሉ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ከታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ ገልጿል”
 
በዚሁ መሰረት የቤንዚን፣ የኬሮሲን፣ የነጭ ናፍጣ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበረው የመሸጫ ዋጋ የሚቀጥሉ ሲሆን፤ የአውሮፕላን ነዳጅ መሸጫ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ 69 ብር ከ82 ሳንቲም እንዲሸጥ የተወሰነ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
Exit mobile version