Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ማሞ ምህረቱ እና ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ከፈረንሳይ ንግድ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ከፈረንይ ንግድ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ መካከል ያለውን የንግድ ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ኦሊቪየር ቤችት÷ ፈረንሳይ በኢትዮጵያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት እደምትደግፍ አረጋግጠዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና በግጭት የተጎዱ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚትደግፍ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
Exit mobile version