Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቀማጭ ገንዘቡ 1 ትሪሊየን ብርን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቀማጭ ገንዘብ በዛሬው ዕለት ከ1 ትሪሊየን ብር መሻገሩን አስታውቋል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ከ1 ትሪሊየን ብር በላይ መሻገሩ ይፋ አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ ባንኩ እዚህ ደረጀ እንዲደርስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት፣ ለባንኩ ደንበኞች እና ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ይህ ገንዘብ ህዝብ በባንኩ ያስቀመጠው የህዝብ ሀብት መሆኑን እና እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱም ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ባንኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

Exit mobile version