Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እንዲዘጋጁ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መውጫ  ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር በሁሉም የትምህርት መስኮች እና መርሐ ግብሮች በግልና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት÷ የመውጫ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡

ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆን ተማሪዎች በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ወሰነ ትምህርት ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

 

 

 

 

 

Exit mobile version