Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቱርክና ሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 17 ሺህን አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰኞ በደቡባዊ ቱርክ እና ሰሜናዊ ሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 17 ሺህ ማለፉ ተገለጸ፡፡

ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ሊኖሩ ቢችሉም፥ መጠለያዎች በመውደማቸው ፣ “የውሃ፣ ነዳጅ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ተጨማሪ ሕይወት ልናጣ እንችላለን” ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ሥጋቱን ገልጿል፡፡

አሁንም ካለፈው የከፋ አደጋ ከፊት ሊኖር ይችላል ብሏል ድርጅቱ፡፡

ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ የጫኑ የተመድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሶሪያ እያመሩ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የነፍሥ አድን ሠራተኞች ተጎጅዎችን በሕይወት ለመታደግ እልህ አስጨራሽ ትግል ላይ መሆናቸውም ነው የተጠቆመው፡፡

በርካቶች የሕንጻ ፍርስራሾች ወድቆባቸው ለሠዓታት በመቆየታቸው በቀጣይ በሕይወት የመገኘታቸው ሁኔታ ተሥፋ አስቆራጭ እንዳደረገውም ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version