Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

ዋና ጸሐፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ሁሴን አብደልባጊ አኮል በ36 የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል።

36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል።

በጉባዔው ላይ ለመሳተፍም ከትናንት ምሽት ጀምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

Exit mobile version