Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶ/ር አለሙ ስሜ እና ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ከጅቡቲ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ከጅቡቲ ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የጅቡቲ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡
በተለይም በሎጂስቲክስ፣ በሪል ስቴት፣ በአግሮ ኢንዱስትሪና በማዕድን ዘርፎች መሰማራት በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን በኢትዮጵያ ከጅቡቲ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version