Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሀገር ሽማግሌዎችበበኩላው÷ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ህዝቦች መካከል አንድነትን በማጠናከር ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

ለተግባራዊነቱም ከመንግሥት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኦስማን፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ ኢንጂነር ሞሃመድ ሻሌ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

Exit mobile version