Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮርፖሬሽኑ 219 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ ምርጥ ዘር ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014/15 የምርት ዘመን ከ15 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በምርጥ ዘር በመሸፈን 219 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ ምርጥ ዘር መሰብሰቡን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡

በዚህም እስከ የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ 218 ሺህ 806 ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ነው ኮርፖሬሽኑ የገለጸው።

የተሰበሰበውን ምርጥ ዘርም በማበጠርና በማዘጋጀት ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በ15 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ በዓመት ከ300 ሺህ ኩንታል በላይ የ21 ሰብሎችን 70 ዝርያዎች በማምረት ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብም ታውቋል።

የመስኖ ልማትን በማስፋፋትና ተጨማሪ መሬት በማፈላለግ ወደ ውጭ የሚላኩ ሰብሎችን ለማምረት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑ የኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ጋሻው አይችሉህም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version