Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓድዋ ድልን ምክንያት በማድረግ አውደ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ሚኒስቴር የዓድዋ ድልን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው አውደ ርዕይ ለዕይታ ክፍት ሆኗል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዴዔታ ማርታ ሉዊጂ እና ከፍተኛ መኮንኖችና የሰራዊቱ አመራሮች አውደ ርዕዩን ከፍተውታል፡፡

እስከ የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም በሚቆየው አውደ ርዕይ÷ ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት ያደረጉትን ተጋድሎ የሚያስቃኝ ዝግጅት መቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለአብነትም÷ በጦርነቱ ወቅት ጦርነቱን የመሩ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ታሪክ፣ ፎቶዎች፣ ለናሙና የቀረቡ ጦር መሳሪያዎች ፣ ዓድዋን በተመለከተ የተደረሱ የስነ ጽሁፍ ስራዎች በአውደ ርዕዩ ቀርበዋል፡፡

እንዲሁም በጣልያን በኩል ጦር መርተው ሽንፈት የገጠማቸው ጄኔራሎች ታሪክ የአውደ ርዕዩ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

Exit mobile version