Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓድዋ ድል በዓል የመላው የጥቁር ህዝብ የጀግንነትና የአንድነት በዓል ነው- አቶ ሙስጠፌ መሐመድ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 20115 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው የጥቁር ህዝብ የጀግንነትና የአንድነት በዓል ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ፡፡

አቶ ሙስጠፌ ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፋዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የዓድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ህዝብ የጀግንነት፣ አንድነትና ለኢትዮጵያውያን ደግሞ የአልገዛም ባይነትና የጀግንነት ደማቅ ታሪክ የተፃፈበት ነው ብለዋል፡፡

አባቶቻችን ከመላው ሀገር ተሰባስበው እና በአንድነት ቆመው አጥንታቸውን ከስክሰውና ደማቸውን አፍስሰው ሀገርን ያፀኑበት በመሆኑ የዓድዋ ድል በዓልን ስናከብር በኩራት ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ለባርነትና ለቀኝ ግዛት አንምበርከክም በማለት ህይወታቸውን ገብረው ለዛሬ ነፃነት የተዋደቁ ጀግኖች ያለፉበት የሁሉም አፍሪካውያን የድል ቀን በመሆኑ ዓድዋን በድምቀት እና በጋራ እናከብረዋለን ነው ያሉት፡፡

Exit mobile version