Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በባህር ዳር የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጀመሩ ተገለጸ።

የኮሮና ቫይረስ ምርመራው በክልሉ የማህበረሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ውስጥ ነው የተጀመረው።

መመርመሪያ መሳሪው ካለው የሰው ሀይል አንፃር በቀን የ100 ሰዎችን ናሙና በመውስድ የሚመረምር መሆኑን በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ገልጸዋል።

በቀጣይም በጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረብርሃን የምርመራ ስራውን ለመጀመር እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከክልሉ አንድ ሴት እና ሁለት ወንዶች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የሚታወስ ሲሆን ሁሉም በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

 

 

በናትናኤል ጥጋቡ

Exit mobile version