Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኦሮሚያ ክልል በተወሰኑ ዞኖች ለተከሰተው ድርቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላት የእውቅ እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተወሰኑ ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሰብዓዊ እርዳታ ላደረጉ አካለት እውቅና የመስጠት ሥነ ስርዓት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡
እስካሁንም በአጠቃላይ 850 ሚሊየን ብር በዓይነትና በገንዘብ መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡
በፈትያ አብደላ
Exit mobile version