Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በትግራይ ክልል ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የኮሮና ቫይረስ የቤት ለቤት ዳሰሳ ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ ሊካሄድ ነው

Mekelle, Ethiopia - October 13: Overview of the city on October 13, 2015 in Mekelle, Ethiopia. (Photo by Thomas Imo/Photothek via Getty Images)

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ የቤት ለቤት ዳሰሳ ከሚቀጥለው ሰኞ ሚያዚያ 5 ቀን 2012 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት እንደሚካሄድ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ እንደገለፁት፥ በዳሰሳው 23 ሺህ የጤና ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።

ህብረተሰቡ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት፣ ለመከላከል የሚያስችል ግንዛቤና በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚመለከት ያለው ግንዛቤ በእያንዳንዱ ቤት ይዳሰሳል ነው ያሉት።

በተጨማሪም ከክልሉ ውጭ የመጡ ሰዎች ካሉ እያንዳንዱን ቤት በመፈተሽ ምርመራ ይደረግላቸዋል።

ሁሉም ባለሙያ በክልሉ ባሉት 92 ወረዳዎች የተመደበ ሲሆን፥ በዚህም በገጠር በቀን ከ15 እስከ 20 እንዲሁም በከተማ ከ25 እስከ 30 ቤቶች ለማጥናት እቅድ ተይዟል ብለዋል።

ዳሰሳው በመቐለ ከተማ ነገ እንደሚጀመር በመጠቆምም ህብረተሰቡ ለዳሰሳው እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

Exit mobile version