Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ የተፈናቀሉ ህፃናትን ማቋቋሚያ ፕሮጄክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ፣ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና አጋሮቹ በኢትዮጵያ በግጭት እና በተለያዩ ምክንያት የተፈናቀሉ ህፃናትን ማቋቋሚያ ፕሮጄክት ይፋ አድርገዋል፡፡

ፕሮጄክቱ በጋምቤላ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች የሚተገበር ሲሆን በግጭት እና በተለያየ ምክንያት የተፈናቀሉ ህፃናትን ለማቋቋም ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ፕሮጄክቱ የአደጋ ተጋላጭነትን በመቀስ ፣ የህፃናትን እንክብካቤን ለማጠናከር እና የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡

Exit mobile version