Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በድንበር አካባቢ የጸጥታ ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሀገራቱ የጋራ ድንበር አካባቢ የሚከሰቱ የጸጥታ ስጋቶችን በቅንጅት ለመከላከል ተስማምተዋል፡፡
 
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ የተመራ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ ከኬንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በናይሮቢ ተወያይቷል፡፡
 
በውይይታቸውም ሀገራቱ በጸጥታው ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሀገራቱ የጋራ ድንበር አካባቢ የሚከሰቱ የጸጥታ ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸውንም ጠቁመዋል፡፡
Exit mobile version