Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነርለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሞርስላቭ ኮሴክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም የሀገራቱን አጋርነት ለማጠናከር በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳች ላይ መምከራቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ባተኮሩ እና ስትራቴጂካዊ በሆኑ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ስራዎች የቼክ ባለሃብቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ በጋራ እንደሚሰሩም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
Exit mobile version