Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የግማሽ ማራቶን ውድድር በደብረ ብርሃን ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሄደ።

በውድድሩ ከሁለት ክልሎች 12 ክለቦች እና ተቋማት እንዲሁም በግል የሚወዳደሩ አትሌቶችን ጨምሮ በወንድ 190፣ በሴት 96 በድምሩ 286 አትሌቶች መሳተፋቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።

በዚህም መሰረት በወንዶች ጫላ ከተማ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ 1ኛ ደረጃ፣ ተሰማ መኮንን ከፌደራል ማረሚያ 2ኛ እንዲሁም ሀብታሙ አብዲ ከኢ/ኤሌክትሪክ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች 1ኛ ደረጃ ዘውዲቱ አደራው ከአማራ ፖሊስ፣ 2ኛ እናትነሽ አላምረው ከአማራ ፖሊስ እንዲሁም መሰረት ጎላ ከኢት/ኤሌክትሪክ 3ኛ ደረጃን በመያዝ የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

 

 

 

Exit mobile version