Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ ከ450 ሚሊየን ብር ባለይ ግምት ያለው ሰብልና ንብረት አወደመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን አምባሠል እና አልብኮ ወረዳዎች የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ምክንያት ከ450 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሰብልና ንብረት ወድሟል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢብራሂም ይመር እንዳሉት÷ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በእንስሳት፣ በመስኖሰብል፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በመኖሪያ ቤት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

በዚህም በ571 ሔክታር መሬት ላይ የነበረ ሰብልን ጨምሮ አትክልትና ፍራፍሬ ሙሉ በሙሉ ወድሟል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም አምስት የቀንድ ከብት፣ 29 በግና ፍየል፣ ሥድስት መኖሪያ ቤት፣ 29 የንብ ቀፎ እንዲሁም 220 ሔክታር የሚያለማ የመስኖ ካናል መውደሙን አብራርተዋል፡፡

ለጉዳቱ የተጋለጡ የህብረተሠብ ክፍሎች አስቸኳይ የዕለት እርዳታ፣ መጠለያ እና አልባሣት እንደሚያስፈልጋቸው ኃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version