Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ፡፡

በጉባዔው የከተማ አስተዳደሩ  ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ  ወይዘሮ ቡዜና አልከድርን ጨምሮ፣  የምክር ቤት አባላት፣ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአስተዳደሩን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

በዚህ ወቅትም ባለፉት ስድስት ወራት የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ውጤታማ ስራዎች ማከናወን እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ስር የሰደዱ የተወሳሰቡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና መዋቅራዊ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ባለድርሻ አካላትንና ህዝቡን በማሳተፍ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል ነው ያሉት።

Exit mobile version