Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቻምፒየንስ ሊጉ ሩብ ፍጻሜ ማንቼስተር ሲቲን ከባየር ሙኒክ ያገናኘው ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡

በድልዱሉ መሰረት የአምናው ሻምፒዮን ሪያል ማድሪድ ከቼልሲ ጋር ተገናኝቷል።

የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ደግሞ ከፖርቹጋሉ ቤኔፊካ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።

የእንግሊዙን ማንቼስተር ሲቲ ከጀርመኑ ሃያል ባየርን ሙኒክ ጋር ያገናኘው ጨዋታ የሩብ ፍጻሜው ተጠባቂ ሆኗል።

የጣሊያኑ ሻምፒዮን ኤሲ ሚላን ደግሞ በዘንድሮው የውድድር አመት በድንቅ ብቃት ላይ ከሚገኘው የሉቺያኖ ስፓሌቲው ናፖሊ ጋር በሩብ ፍጻሜው ተደልድሏል።

የሩብ ፍጻሜው የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሚያዝያ 3 እና ሚያዝያ 4 ቀን ሲካሄዱ፥ የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ሚያዝያ 10 እና ሚያዝያ 11 ቀን ይደረጋሉ።

ግንቦት 1 ቀን በሚጀመረው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የኤሲ ሚላን እና ናፖሊ አሸናፊ ከኢንተር እና ቤኔፊካ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

በአንጻሩ የሪያል ማድሪድ እና ቼልሲ አሸናፊ ደግሞ ከማንቼስተር ሲቲ እና ባየርን ሙኒክ  አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል።

Exit mobile version