Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር )የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ መቆየታቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ ከሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ፡፡

Exit mobile version