Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ16 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ16 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ባለፉት ሰባት ቀናት ተያዙ።

የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ሀሰተኛ ሰሌዳ የለጠፉ 3 ተሽከርካሪዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎች፣ መድኃኒቶች፣ ጥራቱ ያልተረጋገጠ የፊት ክሬም፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቅሽር ቡና፣ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች፣ የምግብ ዘይት፣ አደንዛዥ ፅጽና ሀሺሽ፣ ሲጋራና የተለያዩ ዓይነት ብረታ ብረቶች ናቸው።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ፣ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ፣ ጅግጅጋ፣ ሀረር፣ አዋሽ፣ ሞጆ፣ ሀዋሳ፣ ኮምቦልቻ፣ ወልዲያ፣ ባቲ እና ሌሎች ኬላ ጣቢያዎች የተያዙ ሲሆን፥ እቃዎቹም በህገ-ወጥ መንገድ ሊገቡ እና ሊወጡ ሲሉ መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version