Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን መደገፍ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በዓለም ባንክ ከምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም  እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች ዙሪያ መምከራቸውን ቪክቶሪያ ክዋክዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ዓለም ባንክ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙን መደገፍ በሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውንም ምክትል ፕሬዚዳንቷ ጠቁመዋል፡፡

Exit mobile version