Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሻሸመኔ ከተማ ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

በድጋፍ ሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው፡፡

ከለውጡ በኋላ ባለፉት 5 ዓመታት በክልሉ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊና በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ለውጦችን የሚያሳዩ መፈክሮችንም በማሰማት ላይ ናቸው፡፡

በድጋፍ ሰልፉ በርካታ የሻሸመኔ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው፡

Exit mobile version