Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሕዝበ ሙስሊሙ ከተቸገሩት ጎን እንዲቆም ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ሙስሊሙ እንደ ወትሮው ሁሉ ከተቸገሩት ጎን መቆሙን አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ጠየቀ፡፡

3ኛው ዙር ታላቁ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ ስርዓት “ኢፍጣራችን ለወገናችን” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ በሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የዛሬው ኢፍጣር የሚለየው በተለያየ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች እጃችንን የምንዘረጋበት በመሆኑ ነው ብለዋል።

ሕዝበ ሙስሊሙም እንደ ወትሮው ሁሉ ከተቸገሩት ጎን መቆሙን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት፡፡

ሥነ ስርዓቱ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑንም ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ተናግረዋል፡፡

ሙስሊሙ ማሕበረሰብ አንድነቱን እና ሀገራዊ አብሮነቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል የጎዳና ላይ ኢፍጣሩ ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በመራኦል ከድር

Exit mobile version