Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዋሊያዎቹ በአሜሪካ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ሐምሌ ወር በአሜሪካ የጉብኝት ጉዞ ሊያደርግ  መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡

በዚህም ቡድኑ በፈረንጆቹ ሐምሌ 8 ቀን 2023  ዋሺንግተን እንደሚገኝ  ተገልጿል፡፡

በቆይታውም ከካሪቢያን ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ጨዋታ እንደሚያደርግ ከፌዴሬሽኑ  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዋሽንግተን የሚገኙ የብሄራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች ቡድኑን ለማበረታት እንዲዘጋጁ ጥሪ ያቀረበው ፌዴሬሽን የመግቢያ ትኬቶችን በተመለከተ በቅርቡ ይፋ እንደሚደርግ ገልጿል፡፡

Exit mobile version