Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተመድ የኢትዮጵያን ሠላም አስከባሪ ሠራዊት አመሰገነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት በሶማሊያ እና ቀጣናው ሠላም በማስፈን ረገድ ለተወጣው ሚና አመሰገነ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶማሊያ ባይደዋ ከተማ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎብኝተዋል።

ዋና ፀሐፊው እንዳሉት በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ በሕብረተሰቡ ላይ ያስከተለው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡

ጉብኝቱም ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ጠቀሜታ ማስገንዘባቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

የድርጅቱን ሠራተኞች ደኅንነት በአግባቡ በመጠበቅና ሥራዎችን ከድርጅቱ ሠራተኞች ጋር በማከናወን ላሳዩት ትጋትም አንቶኒዮ ጉተሬዝ ለኢትዮጵያን ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version