Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ሂሩት ከአውሮፓ ሕብረት የአደጋ እና ሰብዓዊ ጉዳዮች ኮሚሽን ዳይሬክተር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በአውሮፓ ሕብረት የዜጎች ጥበቃ እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራዎች ኮሚሽን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ፣ ኢሲያ፣ ላቲን አሜሪካ እና ፓሲፊክ ዳይሬክተር አንድሪያ ኩላይማን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በኮሚሽኑ መካከል ባለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ትብብር ዙሪያ መክረዋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተከናወነ ባለው የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ላይ መምከራቸውንም የኤንባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም በወቅታዊው ድርቅ ሁኔታ፣ በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች እያደረሰ ያለውን ጉዳት በተመለከተ ተወያይተዋል፡፡

በቅርቡም በአውሮፓ ሕብረት በኩል ለኢትዮጵያ ለተደረገው የ60 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አምባሳደር ሂሩት አመስግነዋል።

Exit mobile version