Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለገጣፎ ለገዳዲ ከሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሣምንት ጨዋታ ለገጣፎ ለገዳዲ እና ሀድያ ሆሳዕና በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ዛሬ 9፡00 ላይ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ያለምንም ጎል ተጠናቋል፡፡

12:00 ላይ በተካሄደ ሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ሲዳማ ቡናን 3 ለ1 አሸንፏል፡፡

Exit mobile version