Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ በሱዳን ጉዳይ ከተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በሱዳን አለመረጋጋት ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መክረዋል፡፡

ዋና ፀሐፊው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ ከእንግሊዝ፤ ካናዳ እና ጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይቱም ኢጋድ ሁኔታውን በአንክሮ እየተከታተለው መሆኑን በመግለፅ እያደረገ ካለው የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎት አንፃር ኢጋድ ያለውን ስጋት አጋርቷል ብለዋል።

በሱዳን አፋጣኝ የተኩስ ማቆም፣ ያልተስተጓጎለ የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት እና የሲቪል ማህበረሰቡን ደህንነት ማስጠበቅ ላይ በጋራ ለመስራት ያለንን ቁርጠኝነት አረጋግጠናል ነው ያሉት።

Exit mobile version