Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቻይና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ወደፊት እየተምዘገዘገች መሆኑ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እንደሌሎች ዘርፎች ሁሉ በዲጂታል ኢኮኖሚውም ወደፊት እየተምዘገዘገች መሆኑ ተመለከተ።

ለሁለት ቀናት የተካሄደው ስድስተኛው የቻይና ዲጂታል ጉባዔ፥ ሀገሪቱ ምን ያህል ተጠቃሚ እየሆነችበት እንደሆነ አሳይቷል፡፡

ጉባዔው የተካሄደው በፉጂያን ግዛት ዋና ከተማ ፉዪዡ ሲሆን፥ በዲጂታል ልማት ዘርፍ ምክክሮች ተካሂደውበታል፡፡

በዘርፉ በተሰማሩ የቴክኖሎጂ አበልፃጊዎች እና የንግድ ኩባንያዎች መካከል በርካታ የፕሮጀክት ስምምነቶችም ተከናውነውበታል፡፡

በሁለት ቀናት ቆይታ ብቻ ወሳኝ ናቸው በተባሉ 52 የዲጂታል ኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ላይ የ58 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈረሙን የዘገበው ዥኖዋ ነው፡፡

Exit mobile version